ለዘመቱ፣ ለአቅመ ደካማ እና ወላጅ አልባ ለሆኑ ህጻናት ድጋፍ አድርጓል፡፡
የሰላሌ ዩኒቨርሲቲ የምርምርና ማህበረሰብ አገልግሎት ምክትል ፕሬዝዳንት እሸቱ ወንድሙ (ዶ/ር) ዩኒቨርሲቲው በሰሜን ሸዋ ዞን ለሚገኙ ትምህርት ቤቶች እና ለተለያዩ ሆስፒታሎች የቁሳቁስ ድጋፍ በማድረግ ማህበራዊ ኃላፊነቱን እየተወጣ ነው ብለዋል፡፡
ሰላሌ ዩኒቨርሲቲ የላቀ ውጤት የሚያመጡ ተማሪዎችን ከ9 እስከ 12ኛ ክፍል ሙሉ ወጪያቸውን በመሸፈን የሚያስተምርበት ሸረሮ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤትን በማቋቋም ለነገ ሃገር ተረካቢ ብቁ ዜጋ ለማፍራት እየሰራ መሆኑንም ተናግረዋል፡፡