በምስረታዉ ስነ- ስርዓት ላይ መምህራን፤ ተማሪዎች እንዲሁም የአስተዳደር ሰራተኞች የተገኙ ሲሆን የመክፈቻዉን ንግግር ያደረጉት የዩኒቨርሲቲው ምርምርና ማህበረስብ አገልግሎት ም/ፕሬዝደንት ዶ/ር እሸቱ ወንድሙ ናቸዉ፡፡ የክበቡን ምስረታ አስመልክቶ ዉይይት የተደረገበት የዶ/ር ምህረት ደበበ ʿየተቆለፈበት ቁልፍʾ የተሰኘዉ 439 ገጽ ያለዉ የ2004 እትም መጽሀፍ ሲሆን የዉይት መነሻ ሀሳብ ያቀረቡት የዕለቱ አወያይ የአማርኛና ስነ-ጽሁፍ ት/ክፍል ሀላፊ የሆኑት አቶ ደርብ ጌታቸዉ ናቸዉ፡፡ በዚህ መጽሀፍ ላይ ብዙ የሀሳብ መለዋወጦች ከተደረጉ በኋላ በቀጣይ ለዉይይት የሚቀርቡ መጽሀፍቶችም በተሳታፊዎች ተመርጠዋል፡፡ ይህ ተግባርም በወር እንዴ እንደሚደረግ ተገልጿል፡፡የመዝጊያ ንግግር ያደረጉትም የትምህርት ጥራት ማረጋገጫ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ እንደሻዉ መንግስቱ ናቸዉ፡፡
News
በሰላሌ ዩኒቨርሲቲ ʿገበታ የመጽሀፍ ክበብʾ ተመሰረተ
- Published: 21 May 2019
- Hits: 1191