አጥላዉ እንደገለጹት ዩኒቨርሲቲዉ መምህራን ከማስተማራቸዉ ባሻገር የተለያዩ ፅሁፎችን በመፃፍና በማሳተም የማስተማሪያ መንገዳቸዉን ማስፋት እንዳለባቸዉና እንዲህ አይነት መድረኮችም መለመድ እንዳለባቸዉ አፅንኦት ሰጥተዉ ተናግረዋል፡፡የግጥም መድብሉን ይዘትና የአፃፃፍ ስልት በተመለከተ ጠቅለል ያለ ማብራሪያ የሰጡት የአማርኛና ስነ-ፅሁፍ ት/ት ክፍል ሀላፊ የሆኑት መምህር ደርብ ጌታቸዉ እንደተናገሩት አፃፃፉ አዳዲስ የአፃፃፍ ስልትን የተከተለ መሆኑን ከመድብሉ ዉስጥ በተወሰዱ ማሳያ ግጥሞች ጠለቅና ሰፋ ባለ መልኩ ማብራሪያ በመስጠት የደራሲዉን ችሎታ አሞካሽተዋል፡፡በምረቃዉ ስነ-ስርአት ላይም የተገኙ መምህራን ፣ ተማሪዎች እንዲሁም የአስተዳደር ሰራተኞች ሲሆኑ ለምርቃቱ ማዋዣ የሚሆኑ ግጥሞች ፣ ወጎች እንዲሁም ጉዞ ማስታወሻ በራሱ በደራሲዉና በተሳታፊ መምህራን ቀርቧል፡፡ የኦሮምኛ ቋንቋ ግጥምም ዝግጅቱን ካደመቁት ስነ-ፅሁፎች አንዱነዉ፡፡በመጨረሻም የዩኒቨርሲቲዉ ምርምርና ማህበረሰብ አገልግሎት ምክትል ፕሬዘዳንት በመዝጊያ ንግግራቸዉ የመምህር ዮናስ ስራ ፋናወጊ መሆኑን አዉስተዉ ይህ ጅማሮ እንጂ መጨረሻ አለመሆኑን አስረግጠዉ ተናግረዋል፡፡
News
በሰላሌ ዩኒቨርሲቲ የግጥም መድብል ምረቃ ተከናወነ
- Published: 21 May 2019
- Hits: 1128