Welcome to Salale University’s (SlU) Official Website,It is my great honor to serve as the President of Salale University, and I am deeply inspired to work alongside the dedicated and enthusiastic staff of our institution. I firmly believe that education is the most powerful tool to drive national progress and improve lives in all dimensions. It serves as the foundation for all forms of advancement, achievable only when access and equity are ensured.
With this vision, and guided by our motto, "Co-Creating Quality," Salale University was established in 2015 in Fiche town, North Showa Zone, Oromia Region, located 112 kilometers from Addis Ababa. Since its inception, SlU has been steadfastly committed to its three core missions: education, research, and community service. The University began its academic journey with nine undergraduate programs. Today, it offers more than thirty undergraduate programs, and we have finalized preparations to launch postgraduate programs in various fields by 2020. Our region, North Showa, widely known as "Salale" for historical reasons, is uniquely positioned, bordered by two major tributaries of the Nile River—Mogor and Jama—as well as the Nile itself. This area has attracted significant attention from researchers and academics due to its potential mineral resources.
Read More...| Su | M | Tu | W | Th | F | Sa |
|---|
የሰላሌ ዩኒቨርሲቲ የኃላፊነት ጊዜያቸውን ያጠናቀቁ ዳይሬከተሮች የምስጋና ፕሮግራምና አዲስ ወደ ኃላፊነት ለመጡ የስራ መመሪያ ፕሮግራም አካሄደ፡:
በፕሮግራሙ ላይ የሰላሌ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ፈዬራ ዲንሳና የሰላሌ ዩኒቨርሲቲ የአካዳሚክና የምርምር ጉዳዮች ምክትል ፕሬዝዳንት ዶ/ር ጸጋዬ ደዩ ተገኝተዋል፡፡
የሰላሌ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ፈዬራ ዲንሳ በፕሮግራሙ መርሀ ግብር ላይ በመገኘት ባስተላለፉት መልዕክት ኃላፊነት ደንቦችን እና ግዴታዎችን ማክበር ሲሆን ለውሳኔዎቻችን እና ድርጊቶቻችን ቅድመ ጥንቃቄ መውሰድንና በደንቦቹና በተቀመጠው ህግ መሰረት መስራት እንደሆነ በመግለጽ፣አንድ አመራር አመራር ሆኖ ሲሰራ መከተል ያለበትን የአስተደደር መርሆችን በስፋት ጠቅሰዋል፡፡በስተመጨረሻም የኃላፊነት ጊዜያቸውን ያጠናቀቁ ዳይሬከተሮች ከአዲሶቹ ጎን ሆነው የተቋሙን ስራ ይበልጥ እንዲያስቀጥሉ በማሳሰብ አዲስ ወደ ኃላፊነት ለመጡት ደግሞ መልካም የስራ ዘመን እንዲሆንላቸው ተመኝተዋል፡፡
ከዚህም በተጨማሪ የሰላሌ ዩኒቨርሲቲ የአካዳሚክና የምርምር ጉዳዮች ምክትል ፕሬዝዳንት ዶ/ር ፀጋዬ ደዩ እንደተናገሩት ኃላፊነት የጋራ ግብ ስኬት እና ውጤታማነት ላይ በመስራት ሌሎች እንዲያበረታቱ እና እንዲረዱ የማድረግ ጥበብ እንደሆነ በመጥቀስ፣ አንድ ሰው ወደ ኃላፊነት ሲመጣ የተቋሙን አሁናዊ ደረጃን በቅርበት መከታተልና በማወቅ የስራ ቦታውን ምቹ ሁኔታን በመፍጠር ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር እጅና ጓንት ሆኖ መስራት አስፈላጊ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ በተጨማሪም የኃላፊነት ጊዜያቸውን ያጠናቀቁ ለዩኒቨርሲቲው ትልቅ ሃብት መሆናቸውንና ለወደፊቱም ተቋሙን በተለያዩ የስራ ዘርፍ እገዛ እንደሚያደርጉ በመግለጽ ለቀድሞዎቹ የስራ ኃላፊዎች ምስጋናቸውን ችረዋል፡፡
በዚህ መርሀ ግብር ላይ ተሳታፊዎች ከዩኒቨርሲቲው አመራሮች ጋር በርካታ ነጥቦችን በማንሳት ሰፋ ያለ ውይት ከተደረገ በኋላ፣ የቀድሞ የስራ ኃላፊዎች አዲስ ወደ ኃላፊነት ለመጡ የሰነድ ርክክብ በማድረግ ፕሮግራሙ ተጠናቋል፡፡
>>ሰላሌ ዩኒቨርሲቲ ህዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ሥራ አስፈጻሚ ጽ/ቤት
የካሜራ ባለሙያ:- ሙሉቀን ታፈሰ
ለበለጠ መረጃ።:
YouTube: https://youtube.com/@salaleuniversity5385
• Website: http://slu.edu.et
• X (Twitter): https://x.com/SalaleUniversi1
• Telegram channel: https://t.me/salaleuniversitytchannel