President's Message

President's photo
Contact
Name: Feyera Dinsa (Ph.D)
+251-911235189‬
president@slu.edu.et
+251-111355637
P.O. Box: 245
Administration Building 3rd floor Room 3

Feyera Dinsa (Ph.D)

Salale University President

Welcome to Salale University’s (SlU) Official Website,It is my great honor to serve as the President of Salale University, and I am deeply inspired to work alongside the dedicated and enthusiastic staff of our institution. I firmly believe that education is the most powerful tool to drive national progress and improve lives in all dimensions. It serves as the foundation for all forms of advancement, achievable only when access and equity are ensured.

With this vision, and guided by our motto, "Co-Creating Quality," Salale University was established in 2015 in Fiche town, North Showa Zone, Oromia Region, located 112 kilometers from Addis Ababa. Since its inception, SlU has been steadfastly committed to its three core missions: education, research, and community service. The University began its academic journey with nine undergraduate programs. Today, it offers more than thirty undergraduate programs, and we have finalized preparations to launch postgraduate programs in various fields by 2020. Our region, North Showa, widely known as "Salale" for historical reasons, is uniquely positioned, bordered by two major tributaries of the Nile River—Mogor and Jama—as well as the Nile itself. This area has attracted significant attention from researchers and academics due to its potential mineral resources.

Read More...
News Detail

የሰላሌ ዩኒቨርሲቲ ሥራ አመራር ቦርድ 23ኛ መደበኛ ስብሰባውን አካሄደ፡፡

News Image

በኢፌዴሪ ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ኮሚሽነርና የሰላሌ ዩኒቨርሲቲ የስራ አመራር ቦርድ ሰብሳቢ በክቡር ዶ/ር መኩሪያ ሀይሌ የተመራው የሰላሌ ዩኒቨርሲቲ የስራ አመራር ቦርድ 23ኛ መደበኛ ስብሰባውን አካሂዶ በተለያዩ አጀንዳዎች ዙሪያ በመወያየት ውሳኔዎችን አስተላልፏል።
በኢሊሊ ኢንተርናሽናል ሆቴል በተካሄደው የስራ አመራር ቦርድ ስብሰባ ውይይት የተደረገባቸው ጉዳዮች፡
1. የቀደመውን ቃለ ጉባኤ ማጽደቅ፤
2. የ2017 በጀት ዓመት የስራ እቅድ የአፈጻጸም ሪፖርት
መገምገም፣
3. የ2018 በጀት ዓመት መሪ እቅድ መገምገም፤
4. የተለያዩ አዳዲስ አካዳሚክ ፕሮግራሞችን መገምገም፤
5. ቀድሞ የነበሩትን የሰላሌ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝደንት መሸኘትና
አዲስ የተመደቡትን መቀበል፤
እና ሌሎች ጉዳዮች ላይ በዝርዝር በመወያየት መጽደቅ የሚገባቸውን ገምግሞ ያጸደቀ ሲሆን በመድረኩ የተገኙ የዩኒቨርሲቲው የማኔጅመንት አባላትም በስራ አመራር ቦርዱ የተነሱ ጥያቄዎችና ማብራሪያ የሚያሹ ጉዳዮች ላይ ምላሽና ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡
በውይይት መድረኩ ላይ በዩኒቨርሲቲው ቦርድ እንደተገለጸው ዩኒቨርሲቲው እያከናወናቸው የሚገኙ ተግባራት አበረታች መሆናቸውን የስራ ሀላፊዎች ሲቀያየሩ የስራ ርክክብ ማድረግ ሊለመድ የሚገባው ተግባር መሆኑን በማንሳት ርክክብ የተደረገ መሆኑን በማውሳት ቀድመው የነበሩት የሰላሌ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝደንት ዶ/ር ገናነው ጎፌን ለነበራቸው ቆይታ አመስግነው መልካም እድል እንዲገጥማቸው የተመኙ ሲሆን አዲስ ለተሾሙት ፕሬዝደንት ዶ/ር ፈዬራ ዲንሳ ደግሞ መልካም የስራ ዘመን እንዲሆንላቸው ተመኝተዋል፡፡

Back to list
<